ወላይታ ሶዶ፤ሰኔ 25/2017 (ኢዜአ)፦በአደጋ ጊዜ ለሰብዓዊ ድጋፍ ደራሽ ለመሆን የዝግጁነት አቅምን ማጠናከር እንደሚገባ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ገለጹ።
''ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነትና ለተሟላ ክብር'' በሚል መሪ ሃሳብ ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የአመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር)፤በአደጋ ጊዜ ለሰብዓዊ ድጋፍ ደራሽ ለመሆን የዝግጁነት አቅምን ማጠናከርና ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም በየደረጃው ያለው አመራር በቂ ግንዛቤ ኖሮች ለተግባራዊነቱ በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የሚያስችላት እምቅ አቅምና ሰፊ እድሎች ያሏት መሆኑን ያነሱት ዶክተር መሪሁን፤ በሁሉም መስኮች የተጀመሩ ተስፋ ሰጭ የልማት ጥረቶችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በግብርናም ይሁን በሌሎች ሴክተሮች ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ጥረቶች ተስፋ የተሰነቀባቸው መሆኑን አንስተው፥ በምርታማነት ከእርዳታ ጠባቂነት መውጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በክልሉ ባለፈዉ የበልግ ወቅት ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ በተዘጋጁ መጋዝኖች ምርት የተከማቸባቸው መሆኑን ገልጸው፥በቀጣይም መጠናከር እንዳለበት አንስተዋል።
የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋንታ ጋምአ፤ በክልሉ የሚፈጠሩ አደጋዎችን በራስ አቅም ምላሽ መስጠትና መቋቋም የሚያስችል ዝግጁነት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌማት ትሩፋት፣በበጋ መስኖ ስንዴና በሌሎችም የግብርና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የምርታማነት አቅሞች እየተፈጠሩ መሆኑንም አንስተዋል።
በመድረኩ የክልል፣የዞን፣ የከተማ እና የወረዳ አስተዳደር አመራሮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025