የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በክልሉ የማእድን ፀጋዎችን በአግባቡ በመለየት ጥቅም ላይ ለማዋል የተደረገው ጥረት ውጤት እያመጣ ነው -ቢሮው

Jul 3, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በማዕድን ዘርፍ ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ በመለየት ጥቅም ላይ ለማዋል በተደረገው ጥረት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችል ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የምክክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ አካሂዷል።


የቢሮ ኃላፊው አቶ ሀይሌ አበበ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ በክልሉ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር እየተካሄደ በሚገኘው ጥናት ከ50 ዓይነት በላይ የማዕድን ጸጋዎች እንዳሉ ተረጋግጧል።

የኮንስትራክሽን፣ኢንዱስትሪ፣ብረትና ብረት ነክ፣ የሀይል አማራጭ፣ የከበሩና ሌሎች የማዕድን ፀጋዎችን በመለየት ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዘርፉ እድገትም የማእድን መገኛ ቦታዎችን ለይቶ በማስረከብ፣ ብድር ማመቻቸትና ሌሎችም ድጋፎች በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በዚህም ባለፉት 11 ወራትም 113 ሚሊዮን ዶላር ተኪ ምርት በማምረት ለኢንዱስትሪዎች ግብአት መዋሉን ጠቁመው፥ 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ከዘርፉ ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል።

ዘርፉ ለ48 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠርና ከሮያሊቲና ሌሎች የገቢ አርእስቶች 86 ሚሊዮን ብር ገቢ ማስገኘት መቻሉንም አስረድተዋል።


የደቡብ ወሎ ዞን ማዕድን ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ አበባው በበኩላቸው፥ በዞኑ 33 አይነት ማዕድኖች መኖራቸው በጥናት ተረጋግጦ ወደ ልማት መገባቱንም ገልጸዋል።

ባለፉት 11 ወራትም በማእድን ዘርፍ ለሚሰማሩ ለ325 ባለሃብቶች ፍቃድ መስጠት መቻሉን ጠቁመው፥ ከ5 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል።

በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በቅንጅት በመፍታት የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ማዕድን ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሲራጅ ጀማል ናቸው።


መንግስት በሰጠው ትኩረት በማዕድን ዘርፉ ተኪ ምርት በማምረት፣ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ ለዜጎች የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

በምክክር መድረኩ የክልል፣የደቡብ ወሎ፣የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች፣ እንዲሁም የደሴና የኮምቦልቻ ከተማ አመራሮች፣የዘርፉ ባለሀብቶችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026