
ደብረ ማርቆስ፤ ሰኔ 30/2017 (ኢዜአ)፦ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ ለህዝብ የልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ የበጀት ዓመቱ የገቢ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በደጀን ከተማ ተካሂዷል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ በወቅቱ እንደገለጹት ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ለህብረተሰቡ የልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
ቀደም ሲል በአካባቢው አጋጥሞ በነበረው የጸጥታ ችግር ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ ውስንነት እንደነበር አስታውሰው፣
ችግሩን በቅንጅት ለመፍታት በተደረገ ጥረት የተሻለ ገቢ መሰብሰቡንና የባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦም የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ጥሩምርት አለልኝ እንዳሉት ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
በዚህም በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ የገቢ አርስቶች ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 86 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቅሰዋል።
በየደረጃው ያለው አመራርና የዘርፉ ባለሙያዎች ለገቢ አሰባሰቡ ትኩረት ሰጥተው በቅንጅት መስራታቸው ለብልጫው የራሱን አስተዋጽኦ ማድረጉንም ጠቁመዋል።
ይህም የዞኑን ዓመታዊ ወጭ 22 ነጥብ 6 በመቶ የመሸፈን አቅም እንዳለው ጠቁመው ገቢው ከ37 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል።
በዞኑ የእነማይ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አያሌው መላኩ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በየደረጃው ያለው አመራር ለግብር መሰብሰብ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል።

በበጀት ዓመቱ በወረዳው ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026