🔇Unmute
ዲላ፤ መስከረም 19/2018(ኢዜአ) ፡- በተያዘው ዓመት ቡናን በጥራትና በብዛት በማምረት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለፀ።
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዲላ ቡና ምርት ጥራት ምርመራና ሰርተፍኬሽን ማዕከል ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ማዕከሉ በክልሉ የመጀመሪያው ሲሆን ፤ የንግድ ሰንሰለትን በመቀነስ የቡና አቅራቢውን እንግልት የሚቀንስ መሆኑም ተመላክቷል።
ማዕከሉን መርቀው የከፈቱት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)፤ በተያዘው ዓመት ቡናን በጥራትና በብዛት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ለዚህም የቡና ምርት ጥራት ምርመራና ሰርተፍኬሽን ማዕከላትን ማስፋት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተለይ በልዩ ጣዕሙ የሚታወቀው የይርጋጨፌ ቡናን ተፈጥሯዊ ጣዕሙን ጠብቆ ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።
ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ እንዲሠራ የምርት አቅርቦት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ክልሉ ለቡና ልማት ምቹ ስነምህዳር እንዳለው የገለጹት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ ( ዶ/ር ) ናቸው።
ለዚህም የይርጋጨፌ ፣ አማሮና ሌሎች ቡናዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተው፤ ማዕከሉ የቡና ጥራትን ከማስጠበቅ ባለፈ የምርምርና ስልጠና ማዕከል በመሆን አርሶ አደሩን ማገዝ እንዲችል ይስራል ብለዋል።
በተለይም በቡና ግብይት ወቅት የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት ቀልጣፋ አሰራር መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በበኩላቸው ፤ በዞኑ በቡና እድሳት የተከናወኑ ተግባራት በቡና ምርትና ጥራት ላይ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በዘርፉ የአምራች አርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቀጥታ የውጪ ንግድ ትስስር ተሳትፎውን ለማሳደግ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ማዕከሉ በዲላ ከተማ ሥራ መጀመሩ የንግድ ሰንሰለቱን ቀልጣፋ በማድረግ ለውጪ ገበያ የሚቀርበውን የቡና ምርት መጠን የሚያሳድግ መሆኑን ገልፀዋል።
የማዕከሉ መገንባት ለረጅም ጊዜ ጥያቄያችን ምላሽ የሰጠ ነው ያሉት ደግሞ የጌዴኦ ዞን የቡና አቅራቢዎች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ኢያሱ ወራሳ ናቸው።
በተለይም ማዕከሉ በቅርበት መከፈቱ የተራዘመ የንግድ ሰንሰለትን በመቀነስ የትራንስፖርት ወጪና የጊዜ ብክነትን የሚያስቀር መሆኑን አስረድተዋል።
ማህበሩ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ማዕከሉ የሚጠበቅበትን መስፈርት እንዲያሟላ መደረጉን አንስተው፤ ይህም ማህበሩ ወደ ላኪነት ለማደግ የሚያደረገውን ጥርት ያጠናክራል ብለዋል።
በመረሃ ገብሩ ላይ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ አርሶ አደሮች፣ አቅራቢዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025