🔇Unmute
ወልዲያ፤ጥቅምት 2/2018(ኢዜአ)፦የወልድያ ከተማ የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ግንባታ በመገባደድ ላይ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ንጉስ ዝናቡ፤ በከተማዋ የመጀመሪያው ምእራፍ የኮሪደር ልማት ከአዳጎ አደባባይ በመነሳት እስከ ጎንደር በር ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ላይ አፈፃፀሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አንስተው፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመርቆ ለአገልግሎት የሚበቃ ይሆናል ብለዋል።
የኮሪደር ልማቱ የአስፋልት መንገድ ግንባታና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ አረንጓዴና የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ መሆኑን አንስተው፥ በጥራትና በፍጥነት መከናወኑንም ተናግረዋል።
በዚህም ከ300 በላይ ለሆኑ ወገኖች የስራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን አንስተው፥ ከተማዋን የማልማት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል።
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ፍስሃ መንግስቴ እና ወይዘሮ አልማዝ አያሌው፤ የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ውብና ለኑሮ ምቹ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ልማቱ ለነዋሪዎች፣ ለጎብኝዎች፣ ለባለሃብቶችና ሌሎች አገልግሎት ሰጭዎች ምቹ አካባቢን የፈጠረ በመሆኑ የሚደነቅ ስራ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026