🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2018(ኢዜአ)፦ግብርና የሀገር ኢኮኖሚን በመገንባት፣በመቀየር እና ከማሸጋገር አኳያ ቁልፍ ሚና እየተወጣ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 አፈጻጸም ማጠቃለያ ጉባኤ እና የ2018 የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በዱራሜ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ በ2018 ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ተስፋ ለመሸጋገር የያዘችውን ዕቅድ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሁሉም ዘርፎች የታቀዱ ስራዎች ለውጥ እየታየባቸው መሆኑን ጠቁመው፥ በግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሣካት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በክልሉ በሁሉም ዘርፍ ማለትም በግብርና፣የማኑፋክቸሪንግ ፣በቱሪዝም ፣ በማዕድን ሀብቶችን በአግባቡ መጠቀም እንዲሁም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ግብርና የአገር ኢኮኖሚን መገንባት ብቻ ሳይሆን በመቀየር እና በማሸጋገር ሂደት የሚኖረው አበርክቶ የላቀ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

የቤተሰብ ብልጽግናን በገጠር እና በከተማ ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ካላቸው ዘርፎች ውስጥ ግብርና ወሳኝ ሚና እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ተረጂነትን ለማስቀረት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸውን ጠቁመዋል።
በግብርና ወጪ ምርቶችን በብዛትና ጥራት ማምረት፣ ገቢ ምርቶችን ለመተካት እንዲሁም በዘርፉ የሥራ ዕድል ፈጠራን እውን ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችም ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025