🔇Unmute
አምቦ፤ መስከረም /2018 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ሸዋ ዞን በመኸር ወቅት ከ16 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በቅባት እህል ልማት ላይ መሳተፋቸውን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በዞኑ በመኸር ወቅት በቅባት እህል ዘር ከተሸፈነው ከ31 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከ954 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል፡፡
በጽህፈት ቤቱ የአዝዕርት ልማት ባለሙያ አቶ ደጀኔ ደቡሼ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ በመኸር ወቅት ለቅባት እህሎች ትኩረት በመስጠት ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል።
በዚህም በመኸር ወቅት ከ16 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ ከ31 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በቅባት እህል ማልማት መቻሉን ገልጸዋል።
የቅባት እህል ምርቱ ባለፈው ዓመት በመኸር ወቅት ከለማው ብልጫ እንዳለው ጠቁመው ከዚህም ከ954 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም አቶ ደጀኔ ተናግረዋል።
አርሶ አደሮቹም ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎችን እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባለፈ የግብርና ባለሙያ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
በተጨማሪም ዘርፉን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከግብርና ምርምር ማዕከላት የተለቀቁ የተሻሻሉ የቅባት እህል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጩና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።
እየለሙ ካሉ የቅባት እህሎች መካከል ኑግ፣ ተልባ፣ ሰሊጥ፣ ጎመን ዘርና ለውዝ በስፋት እንደሚገኙበትም ጠቅሰዋል፡፡
የቅባት እህል ምርቱ በዞኑ በተለይም በባኮ፣ በጮቢ፣ በግንደ በረት፣ በኢልፈታ፣ በጀልዱና በኖኖ ወረዳዎች በስፋት እየተመረተ መሆኑም ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025