🔇Unmute
አዳማ ፤ጥቅምት 6/2018 (ኢዜአ)፡-በበጀት ዓመቱ 11 ሚሊዮን የዓሣ ጫጩቶችን በማሰራጨት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ትኩረት መሰጠቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሣ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት የሌማት ትሩፋት ፕሮግራምን በማጠናከር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ስርዓተ ምግብን እውን ለማድረግ ወደ ተግባር ተገብቷል።
በዚህም ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ የዓሣ እርባታ ሥራ መሆኑን ገልጸው፣ ሥራው በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ሐይቆች እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ 11 ሚሊዮን የዓሣ ጫጩቶችን በማሰራጨት 320 ሺህ ቶን አሣ ለማምረት ግብ መጣሉን ተናግረዋል።

ዕቅዱን ለማሳካት የአሣ ጫጩት ማስፋፊያ ማዕከላት በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች እየተገነቡ መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ሙቀትና ቅዝቃዜን የሚቆጣጠር ዘመናዊ የአሣ ጫጩት ማመላለሻ ማሽኖች ለክልሎች መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።
የንጋት ሐይቅን ጨምሮ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሐይቆች እንዲሁም በአርሶ አደሩ ቀዬ በሚሰሩ ኩሬዎች የአሣ ጫጩቶች የማስገባት ሥራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ከሐይቆችና ኩሬዎች አሣን በአግባቡ ለመሰብሰብም ዘመናዊ የዓሣ ማስገሪያ መረቦችና ጀልባዎች ለክልሎች እንዲሰራጩ መደረጉን ነው ፍቅሩ (ዶ/ር) የገለጹት።
በዚህም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትና እና ሥርዓተ ምግብን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026