🔇Unmute
ነቀምቴ ፤ ጥቅምት 12/2018 (ኢዜአ)፦በምስራቅ ወለጋ ዞን የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ቡና አምርቶ ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
በዞኑ በቡና ምርት ላይ ተሰማርተው ለሚገኙ ባለሀብቶች እና አርሶ አደሮች በቡና ምርት ጥራት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
በዚሁ ወቅት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደሱ ለሚ እንደገለጹት በዞኑ የሚገኙ ቡና አምራቾች ከባህላዊ የቡና አመራረት ስልት ወጥተው ጥራት ያለው ቡና ማምረት እንዲችሉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።
አምራቾቹ በሚያመርቱት ቡና ለራሳቸውም ሆነ ለአገር የተሻለ ገቢ ማስገኘት እንዲችሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአመራረት ስልትን እንዲከተሉ ከግንዛቤ ማሳደግ ጀምሮ እስከ ግብዓት አቅርቦት ድረስ ድጋፎች እየተደረጉ ነው ብለዋል።
በተለይም ከቡና ጥራት ጋር የተያያዙ ችግሮች በአብዛኛው ከግንዛቤ እጥረት ጋር የሚያያዙ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን ለመፍታት ከአምራቹ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም የቡናን ጥራት ማስጠበቅ ላይ ተግዳሮት እየሆነ የሚገኘውን ህገወጥ የቡና ንግድን ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ደረጄ ብርሀኑ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዞኑ ከ342 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና እየለማ ይገኛል።

ባለፈው ዓመት ከዞኑ 119 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ የቀረበ ሲሆን በዘንድሮው የምርት ዘመንም ወደ 292 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበው ቡና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ከቡና አምራች ባለሀብቶች እና አርሶ አደሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የተሰጠው ስልጠናም በቡና ምርት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መለየት፣ ደረጃውን የጠበቀ እና ለቡና ገበያ ተፈላጊ ምርት ማቅረብ እንዲሁም የቡና ብክነትን ለመቀነስ እንደሚረዳም አስረድተዋል።
በስልጠናው ላይ ከተሳተፉ ቡና አምራች አርሶ አደሮች መካከል አቶ ዋጂራ ሰንበታ፤ የቡና ጥራት ሲጨምር ገቢን የሚያሳድግ በመሆኑ ለቡና ጥራት ትኩረት መስጠታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025