🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ስኬታማ ድርድር በማካሄዷ እስከ አራት ነጥብ አምስት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚሆን የዕዳ ሽግሽግ ለማስደረግ መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያቸው እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ያለባትን ዕዳ ጫና በንጽጽርና በቁጥር ማየት አስፈላጊ ነው።
በአፍሪካ አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ የሚባሉ ኢኮኖሚዎች ከኢትዮጵያ በብዙ እጥፍ ዕዳ እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ የኢትዮጵያ የዕዳ ጫናም ከ23 ቢሊዮን ዶላር እንደማይበለጥና በንጽጽር ሲታይም ያን ያክል አስደንጋጭ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ዕዳ መጥፎ የሆነው የተወሰደበት መንገድ መሆኑን አብራርተው፤ አብዛኛው ብድር በአጭር ጊዜ መክፈል የሚጠይቅ የኮሜርሻል ብድር ሥርዓት ስለሆነ የኢትዮጵያ ጥያቄ መሸጋሸግ አለበት የሚል መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ባደረገችው ድርድር ከ4 እስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የእዳ ሽግሽግ እንደተደረገ ጠቁመው፤ ይህም ሪፎርሙ ያስገኘው ታላቅ ድል መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ብድር ለመክፈል ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለባት አስታውቀው፤ ለውጡን ተከትሎም መንግስት አንድም ዶላር የኮሜርሻል ብድር እንዳልወሰደ ተናግረዋል።
ከሪፎርሙ በፊት በዚህ ከቀጠለ እንቸገራለን የሚል ስጋት የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ዕዳ ለማስተዳደር ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለባት አስገንዝበዋል።
በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ የሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025