🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ከዘልማዳዊ የአመራረት ዘዴ በመውጣት ቡና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በጥራትና በብዛት እየተመረተ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገለጸ።
በቡና ምርትና ምርታማነት እንዲሁም ጥራት ላይ እየታየ ያለው ለውጥ የተቀናጀ ሥራ ድምር ውጤት መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
በዓለም ከፍተኛ ቡና አምራች ተብለው በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ አምስት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።
የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና በዓለም ተወዳጅ እና ተፈላጊ ነው።
የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት የጀርባ አጥንትና የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆነውን ቡና በብዛትና በጥራት በማምረት ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን የተለያዩ ሥራዎች ተጀምረዋል።
መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ በተለይም ለቡና ጥራትና ምርታማነት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ባለው ሥራ ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙ መጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሰሞኑን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሲሰጡ ይህንኑ አረጋግጠዋል።
እንደ እርሳቸው ገለጻ፣ ከለውጡ ዓመታት ማግስት ኢትዮጵያ በዓመት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ቡና ያመረተች ሲሆን ከወጪ ንግዱ 700 ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች።
በ2017 በጀት ዓመት 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ቡና መመረቱን ገልጸው፤ ከወጪ ንግዱም 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታጋይ ኑሩ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ከዘልማዳዊ የአመራረት ዘዴ በመውጣት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ቡና በጥራትና በብዛት እየተመረተ ነው ብለዋል።
ቀደም ሲል የተንዛዛ የነበረውን የቡና የግብይት ሥርዓትም በፖሊሲ የተደገፈ ማሻሻያ መደረጉን ገልጸዋል።
በዚህም በቡና ምርትና ምርታማነት ላይ ከመጣው ለውጥ ባለፈ ከወጪ ንግዱ የሚገኘው ገቢ ከፍተኛ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ የተሻሻሉ ዝርያዎችን ከመጠቀም ባለፈ ያረጁትን በዘመናዊ መሳሪያዎች እየተጎነደሉ በአዲስ እየተተኩ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዘሪሁን ቃሚሶ በበኩላቸው፤ ማኅበሩ በቡና አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች እንዲፈቱና የቡና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ለማስቻል መቋቋሙን ተናግረዋል።
ከለውጡ በፊት ቡና ላኪዎችም ሆኑ አቅራቢዎች ከ94% በላይ ቡና አምራች የሆነውን አርሶ አደር በቴክኒክና በዕውቀት የመደገፍ አዝማሚያ እንዳልነበርም አንስተዋል።
ይህም አርሶ አደሩ ቡናን በብዛትና በጥራት እንዳያመርት ከማድረግ ባለፈ ከምርቱ ተገቢውን ጥቅም እንዳያገኝ ማድረጉን ተናግረዋል።
ማኅበሩ የቡና ልማትን ሥራ በጥናትና ምርምር እንዲታገዝ ሥርዓተ ትምህርት ከመቅረጽ ባለፈ ከዘር ዝግጅትና አቅርቦት ጀምሮ ለቡና ጉንደላ የሚሆኑ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለአርሶ አደሩ እያከፋፈለ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በፖሊሲና ...
May 20, 2026
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ...
May 7, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋ...
May 7, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት...
Apr 24, 2026