🔇Unmute
ሐረር ፤ ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ)፡-በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማበረታታት ድጋፍና ክትትሉን ማጠናከሩን የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገለጸ።
የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሃምዲ ሰላህዲን ለኢዜአ እንደተናገሩት በክልሉ የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማበረታታት የድጋፍና ክትትል ስራ ትኩረት ተሰጥቶታል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 32 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን ጠቅሰዋል።
የኢንቨስትመንት ፍቃድ የተሰጣቸውም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በአገልግሎት ዘርፎች መሆኑን ተናግረዋል።
የኢቨስትመንት ስራውን ውጤታማነት ለማሳደግ የድጋፍና ቁጥጥር ስራዎችን በማጠናክር በተገቢው ወደ ስራ ያልገቡ 40 አልሚዎች ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ እስከ ኢንቨስትመንት ፍቃድ የመሰረዝ እርምጃ መወሰዱን አመልክተዋል።
እርምጃ ከተወሰደባቸው ባለሐብቶች መካከል 17ቱ በገቡት ውል መሠረት ያላለሙ እና መሬት ተረክበው ወደ ስራ ያልገቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሌሎች ያለ በቂ ምክንያት ግንባታ ያቋረጡና ያለ ግንባታ ፈቃድ ስራ የጀመሩ 18 አልሚዎች ደግሞ እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የድጋፍ ስራዎች ተደርጎላቸው እና መሬት ተረክበው አጥረው በተቀመጡ የአምስት አልሚዎች ፍቃድ መሰረዙን ገልጸዋል።
በቀጣይም በኢንቨስትመንት ፍቃድ መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ አልሚዎች ላይ ክትትል በማድረግ ተገቢውን እርምጃ የመውሰዱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026