🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2018(ኢዜአ)፡-በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለንን የዲጂታል ክህሎት ለማወቅ እየተጋን ነው ሲሉ በመዲናዋ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ።
የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ የስልጠና መርኃ ግብር የዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ ፕሮጀክት ነው።
ይህም የቴክኖሎጂ እውቀት በማበልጸግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ብቃት እንዳስጨበጣቸው መርኃ ግብሩን ተከታትለው የጨረሱ ሰልጣኞች በተደጋጋሚ ገልጸውታል።

መርኃ ግብሩ ዜጎች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዳታ ሳይንስ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግና በዌብ ፕሮግራሚንግ ወሳኝ እውቀትንና ክህሎትን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ሳምንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም አሁን ላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና መውሰድ መቻላቸውን አስታውቀዋል።
መንግሥት ያመቻቸውን እድል በመጠቀም ስልጠናውን እየወሰዱ ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ተማሪዎች ተጠቃሽ ናቸው።
ተማሪዎቹ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በቂ የሆነ የዲጂታል እውቀትና ክህሎት የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
በኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አቤኔዘር ዘገዬወርቅ ስልጠናው ከመደበኛ ትምህርታችን ጎን ለጎን የዲጂታል አቅማችንን እንድናጎለብት አስችሎናል ብሏል።
ከቀረቡት መርኃ ግብሮች መካከል በዌብ ፕሮግራሚንግ እና ዳታ ሳይንስ ስልጠና መውሰዱን ገልጿል።
ያገኘው ስልጠና ጊዜው የሚጠይቀውን የዲጂታል እውቀት እንዲገበይ እንዳደረገው በመግለጽ ቀሪዎቹን የኮደርስ የስልጠና መርኃ ግብሮች በቀጣይ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ጠቅሷል።
በስልጠናው በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተሻለ ክህሎት ማግኘቷን የገለጸችው ደግሞ የብርሃን ጉዞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ህይወት ተስፋሁን ናት።
አርቴፌሻል ኢንተለጀንስ በተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራት ትፈልግ እንደነበረ በመጠቆም መርኃ ግብሩ ፍላጎቷን እውን እንድታደርግ እንዳስቻላት ገልጻለች።
በኮከበ ጽባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሀናን ኢብራሂም በበኩሏ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ስልጠና መውሰዷ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በቀላሉ ለመረዳት እንዳስቻላት ጠቅሳለች።
የብርሃን ጉዞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ኪሩቤል ሀብተስላሴ ዲጂታል ቴክኖለጂውን በሚገባ ለመረዳት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሶ ስልጠናው ክህሎቱን ለማጎልበት እንዳስቻለው ተናግሯል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ቢሮው ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ተማሪዎች የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ከ2017 ጀምሮ ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎች የኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
ቢሮው የዲጂታል እውቀትና ክህሎት የተላበሰ ትውልድ ለመፍጠር የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ስልጠናውን የተከታተሉ ተማሪዎች ወጣቶች ከመደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን የኮደርስ ስልጠናን በመውሰድ ያላቸውን የዲጂታል ህሎት እንዲያጎለብቱ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025