የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ ነው

Nov 6, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ/ጂንካ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።

የባህር በር የማግኘት ጥያቄው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የአንድን ሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራትን የተሰሚነት ተፅዕኖ በአዎንታዊ መልኩ እንደሚያሳድገው በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ይገልፃሉ።

የባህር በር ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት ዕድልን ከማስፋቱም ባሻገር የአንድን ሃገር ዳር ድንበር ተከብሮ እንዲኖር የሚኖረው ሚና ቀላል አይደለም።

ይህና ሌሎች ጉዳዮች ከግምት ሲገቡ ኢትዮጵያ በተሸረበባት ሴራና በልዩ ልዩ በደሎች ከባህር በር እንድትርቅ የተደረገበት ሁኔታ እጅግ የሚያስቆጭ ጉዳይ ነው።

ሆኖም አሁን በኃላፊነት ላይ ያለው መንግስት የበርካታ አመታት የህዝቡ ቁጭት የነበረውን የባህር በር ባለቤትነት አጀንዳን የህልውና ጉዳይ በማድረግ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው እያደረገ ያለበት ሁኔታ ይበል የሚያሰኝ ነው።

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ሃሳባቸውን እንዲያንፀባርቁ እንዲሁም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄና እያደረገች ባለችው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተመለከተ ኢዜአ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ቆይታ አድርጓል።

ምሁራኑ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ ጥያቄ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አበሻ ሺርኮ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ካሉ ተጨባጭ እውነታዎች አንፃር ህጋዊና በግልጽ የቀረበ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል።

የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄው የህልውና ጉዳይ ሆኖ ህጋዊነትን፣ ታሪክንና መልክዓ ምድርን መሰረት በማድረግ የጋራ ተጠቃሚነትን በማለም የተነሳ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ክፍል የሰላምና ደህንነት ትምህርት መምህርና ተመራማሪ ወንድሙ አዴ፤ ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና መቆየቷ ብዙ ዋጋ አስከፍሏል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር የወጣችበት ምክንያት ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት ያልተገኘለትና ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው መሆኑም ለሁላችንም ጥያቄ ሆኗል ብለዋል።

የባህር በር የማግኘቱ ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊ ጥያቄ በመሆኑ ተገቢ የሆነ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በመልክአ ምድር፣ በህግም ይሁን በታሪክ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆን ይገባል ሲሉ የህግ ምሁራን ተናግረዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በጅንካ ከተማ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የህግ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በመልክአ ምድር፣ በህግም ይሁን በታሪክ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የህግ አማካሪና አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ሙሉአለም ኃይለማርያም፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ እውነታን የያዘ በመሆኑ ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አስረድተዋል።

በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የባህላዊ መብቶች የቃል ኪዳን ስምምነት ላይ ሁሉም ሀገራት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል ።

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን የመጠቀም ታሪካዊ፣ ህጋዊ፣ መልካአ ምድራዊ መብት ያላት መሆኑን አስረድተዋል።

ሌላኛው ዐቃቤ ህግ እና የህግ አማካሪ ቢንያም አያሌው፤ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደሚያሳየው የሀገሪቱ ስልጣኔና ሌሎች የመንግስት አደረጃጀቶች በዘመናት መካከል ከባህር በር ተለይተው የማያውቁ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ህጋዊ መሰረት በሌለበት መንገድ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ በህግ አግባብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸው፤ ህጋዊ ስምምነት እስከሌለ ድረስ የባህር በር ባለቤት የመሆን መብቷ የተከበረ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025