🔇Unmute
ጭሮ ፣ጥቅምት 26/2018 (ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በመኽር ወቅቱ ከለማው በርበሬ ከ720 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በጽህፈት ቤቱ የቡና ሻይ እና ቅመማ ቅመም ልማት ቡድን መሪ አቶ ኦሉማ በዳኔ እንዳሉት በዞኑ በመኸር አዝመራ በ15 ወረዳዎች 34 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በርበሬ ለምቷል።
በዞኑ ምርቱ በስፋት በሚካሄድባቸው የሀዊ ጉዲና ፤ ጭሮ፤ ዳሮ ለቡ፤ ገመቺስ ፤ሀብሮ ፤ኦዳ ቡልቱም እና ቦኬ ወረዳዎች የምርት ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በዚህ ዓመት ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ምርት ካለፈው ዓመት ከአስር ሺህ ኩንታል በላይ ብልጫ እንደሚኖረው ነው ያመለከቱት፡፡
በዞኑ የበርበሬ አኒሼቲቭን ለማሳካት አርሶአደሩ ልማቱን በክላስተር በማልማት በጋራ እንዲሳተፍ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡
አርሶአደሮች ለምርት ጥበቃና እንክብካቤ ትኩረት እንዲሰጡ በተደረገው ድጋፍና ክትትል በሄክታር የምርታማነት መጠኑን ከ16 ኩንታል ወደ 20 ኩንታል ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክተዋል፡፡
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን 15 ወረዳዎች እየተካሄደ ባለው የበርበሬ ልማት ከ55 ሺህ በላይ አርሶአደሮች እየተሳተፉ መሆኑም ተመልክቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025