🔇Unmute
ሆሳዕና ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበጀት ዓመቱ በበጋ መስኖ ግብርና ልማት ከ148 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለፀ፡፡
የክልሉን የበጋ ወቅት የመስኖ ልማት ስራ በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምይርጋ ወልደስላሴ እንደገለፁት፡- በክልሉ በበጋ መስኖ ከ148 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

በአብዛኛው በሆርቲካልቸር ሰብሎች ላይ በማተኮር እንደሚሰራ ተናግረው ከ37 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ ወደ ተግባር ስለመገባቱም ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ስኬት ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ መዋቅሮች የንቅናቄና የተግባቦት መድረክ ተፈጥሮ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ስለመገባቱም ነው ያስረዱት፡፡
የመኸር ምርት መሰብሰብ የተጀመረባቸው አካባቢዎች የእርሻ ስራን ጨምሮ ለበጋ መስኖ ግብርና ስራው ትግበራ የሚረዱ ድጋፎች እየተደረገ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡
በክልሉ በሁለት ዙር በሚለማው የበጋ መስኖ ግብርና ልማት ስራ ያሉትን የውሃ አማራጮች ለመጠቀም የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር ስለመገባቱም ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡
የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አህመዲን በበኩላቸው ፡በዘንድሮው የበጋ መስኖ ግብርና ልማት ስራ ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በመሸፈን ከ 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል፡፡

በዞኑ ያሉትን የውሃ አማራጮች ከመጠቀም በተጨማሪ አርሶ አደሩ ድረስ በመዝለቅ በቂ መግባባት ተፈጥሮ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ምርት መሰብሰብ በተጀመረባቸው አካባቢዎች 4 ሺህ ሄክታር መሬት መታረሱንም ገልፀዋል።
በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በግል የእርሻ ልማት ስራ የተሰማራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ስዩም ኃይለጊዮርጊስ በበጋ መስኖ ልማት ስራ የተለያዩ ሰብሎችን ለማልማት ታቅዶ የመሬት ዝግጅትን በማጠናቀቅ ወደ ዘር ስራ እየተገባ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም የአትክልትና የቅባት እህሎችን ጨምሮ ስንዴን በበጋ መስኖ በማልማት ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ሰብሎችን በስፋትና በጥራት ለማምረት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025