የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በኬኒያ የተለያዩ አካባቢዎች እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በርካቶችን ከቄያቸው አፈናቀለ

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ህዳር 22/2017(ኢዜአ)፦በኬኒያ የተለያዩ አካባቢዎች እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በርካቶችን ከቄያቸው ማፈናቀሉ ተገለጸ።


የኬንያ መንግስት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ተጨማሪ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።


በኬኒያ የተለያዩ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ከባድ ዝናብ እየጣለ ነው።


የአደጋ ምላሽ ቡድን አባላት በሚጥለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በደረሰው የጎርፍ አደጋ የተጎዱ ከ240 በላይ አባወራዎችን አደጋ ከደረሰበት ሥፍራ ማንሳት መጀመራቸውን የሀገር ውስጥና ብሔራዊ አስተዳደር ሚኒስቴር በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በሰጠው መግለጫ ማስታወቁን ዥንዋ ዘግቧል።

ሚኒስቴሩ በቪክቶሪያ ሀይቅ ተፋሰስ እና በሰሜን ምዕራብ ክልሎች ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ የጎርፍ አደጋ መከሰቱን በመግለጫው አስታውቋል።

"የአደጋ ምላሽ ቡድኑ ከብሔራዊ የመንግስት አስተዳደር ጋር በመተባበር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለውን ሁኔታ በመከታተል ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እየሰጡ ነው" ሲል ዘገባው አመልክቷል።

በሳምንቱ መጨረሻ እርጥበት አዘል አውሎ ነፋሶች ይጠበቃል ሲል ያመለከተው ዘገባው፤ የሰሜን እና ምስራቃዊ ኬንያ እንዲሁም የባህር ዳርቻ እና የስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የጎርፍ ማስጠንቀቂያዎች መሰጠታቸውንም አክሏል።

ይሁን እንጂ በሚቀጥለው ሳምንት ዝናቡ ሊቀንስ የሚችልባቸው ሁኔታዎች እንደሚኖሩ የሚኒስቴሩን መግለጫ ጠቅሶ ዥንዋ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በተጨማሪም ሀይቅ ዳር በሆነችው ኪሱሙ 200 የሚጠጉ አባዎራዎች መጎዳታቸውን አመልክቶ፤ 100 ሄክታር ማሳ ላይ የተዘሩ ሰብሎች መውደማቸውን ጠቁሟል።

"ለደህንነታቸው ሲባል ለጊዜው ወደ ሌላ ቦታ የሚዘዋወሩ የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢ ነዋሪዎች የአደጋ ምላሽ ከሚሰጡ ቡድኖች ጋር እንዲተባበሩ ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን" ዘገባው አመክቷል።

2024 መጀመሪያ ላይ የጣለው ያልተለመደ ዝናብ ኤልኒኖ ተብሎ ከሚጠራው የአየር ሁኔታ ጋር ተዳምሮ ለአየር ንብረት ለውጥ በጣም ተጋላጭ በሆነችው በኬንያ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን ዘገባው አስታውሷል።

በኬኒያ በመጋቢት እና ሰኔ መካከል በጣለው ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ ከ300 በላይ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ያመለከተው ዘገባው፣ በዚህ ወቅት 188 ሰዎች ቆስለዋል፣ 38 የሚሆኑት ሌሎች ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው መጥፈቱን ዘገባው ጠቁሟል።

በነዚሁ ጊዚያት በጎርፉ ምክንያት ከ293 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ተፈናቅለው ወደ 306 ሺህ 520 የሚጠጉ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ከብሔራዊ የአደጋ መከላከል ማእከል ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ዥንዋ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025