የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

Feb 28, 2025

IDOPRESS

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመሆናቸው ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ መሸጋገራቸውን ገለጹ።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ አንቀሳቃሾች መካከል በሚዛን አማን ከተማ ከሁለት ዓመት በፊት በጫኝ አውራጅ ሥራ 23 አባላትን ይዞ የተደራጀውና ወደሥራ የገባው "ጥምረት ማኅበር" አንዱ ነው።

የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት ፓርቲ አርዱ እንደገለጸው፥ ማህበሩ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በመቆጠብ በአሁኑ ወቅት ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝነት አድጓል።

የማህበሩ አባላት በራሳቸው ፍላጎት ሽግግር ያደረጉት በአራት የተለያዩ የሥራ ዘርፎች በመሰማራት መሆኑን ጠቅሶ "ፍቅር የደረቅ እንጀራ ማኅበር" አንዱ መሆኑን ተናግሯል።

ተደራጅቶ መሥራት ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ በራሳችን ሰርተን ባገኘነው ውጤት አረጋግጠናል ያለው ወጣቱ፣ውጤታማ በመሆናቸው ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ መሸጋገራቸውን ገልጿል።

ለደረቅ እንጀራ አቅርቦት ሥራቸው የሚሆን ከ500 ሺህ ብር በላይ ወጪ የመሥሪያ ቁሳቁስ ማሟላታቸውን ተናግረዋል።

በደረቅ እንጀራ ማኅበር የታቀፉ ስድስት አባላት መሆናቸውን የገለጸው ወጣቱ፥ ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለዘጠኝ ተጨማሪ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ተናግሯል።

በአሁኑ ወቅት ማህበሩ በሚዛን አማን ከተማ ለሚገኙ ሆቴሎች ደረቅ እንጀራን እያቀረበ ሲሆን በቅርቡም ለሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሌሎች የተደራጁ ወጣቶችም አቅማቸውን በማሳደግና ወደ ተሻለ ደረጃ በመሸጋገር ቦታውን ለተተኪዎች መልቀቅ እንዳለባቸው መክሯል።

ከጥቃቅን ወደ ታዳጊ መካከለኛ አንቀሳቃሽነት ከተሸጋገሩት ማህበራት መካከል ደግሞ "ጎዶልያስ የጨርቃ ጨርቅ ማኅበር" አንዱ ነው።

የማኅበሩ ሰብሳቢ ወጣት ጸጋዬ ሳህሉ፥ ማኅበሩ በ15 ሺህ ብር ካፒታል ሥራ መጀመሩን አስታውሶ፥ በአሁኑ ወቅት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራቱን ተናግሯል።

ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝነት ሲሸጋገሩ ከከተማ አስተዳደሩ ባገኙት 500 ካሬ ሜትር የመሥሪያ ቦታ ላይ ሥራውን ለማስፋፋት የሚያስችል የግንባታ ሥራ መጀመራቸውንም ጠቅሷል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ሥራ፣ክህሎት፣ንግድ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምትኩ ጢሞቴዎስ በበኩላቸው፥ በበጀት ዓመቱ 10 ኢንተርፕራይዞች ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ ደረጃ ተሸጋግረዋል።

ለዚህም ከከተማ አስተዳደሩ 1 ሺህ ካሬ ሜትር የሚጠጋ የመሥሪያ ቦታ ለኢንተርፕራይዞች መተላለፉን ገልጸው፥ በተጨማሪም 25 የመስሪያ ኮንቴነሮችን እያዘጋጀን ነው ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ለ21 አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ካፒታል በመመደብ ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉንም ጠቅሰዋል።

በሥራ ዕድል ፈጠራም ከ1 ሺህ 100 ለሚበልጡ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸው፥ የክትትልና ድጋፍ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025