Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ እና የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ገለጹ።
በዩኒቨርሲቲው ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ተቋሙ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል ።
የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ፥ ቦንጋ ዩኒቨርስቲ በመማር ማስተማር ፣በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት እያከናወነ ያለውን ተግባር ለሌች ተቋማት ማካፈል እንዳለበት ተናግረዋል።
የሰው ኃብት ልማት፣ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖልጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ቦንጋ ዩኒቨርስቲ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ እንዲሆን ያስቻለው ጠንካራ አመራርና ሰራተኛውም የቡድን መንፈስ ያለው በመሆኑ ነው ብለዋል።
ለተግባር ተኮርና ችግር ፈቺ ለሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ትኩረት መሰጠቱን በጥንካሬ ያነሱት ሰብሳቢው በመምህራንና በተማሪዎች የሚሰሩ ምርምሮች ወደ ተግባር በመቀየር የአከባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት በማሳደግ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በምርምር የተደገፉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው እንዲሁም ተሞክሮውን ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማስፋት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ለወጣቶችና ለአርሶ አደሩ ስልጠናዎችን በመስጠት የአመለካከት ለውጥ ማምጣትና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በየደረጃው ካሉ የመንግስት አካላት ጋር በጋራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጴጥሮስ ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በመማር ማስተማር ፣በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት በዩኒቨርስቲው የተከናወኑ ተግባራትን ለቋሚ ኮሚቴዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአትክልትና ፍራፍሬ በአካባቢው የአየር ሁኔታ ምክንያት አይበቅሉም የሚለውን ሀሳብ ወደ ጎን በመተው በምርምር የተደገፈ ስራ በመስራት በሙዝ፣በአናናስ በአቮካዶና በሌሎችም የተሻለ ምርት እና ገቢ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው 9 የምርምር ትኩረት መስኮች እና 22 እርሻ ላይ የተመሰረቱ የምርምር ስራዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል።
በምርምር የተገኙ ውጤቶችን ለአርሶ አደሩና ለአካባቢው ህብረተሰብ የማድረስ ስራዎች በስፋት እየተሰራ መሆኑንም ከምክር ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025