
አዲስ አበባ፤ ጥር 1/2017(ኢዜአ)፡- ሀገር በቀል ህንጻ ተቋራጮች ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ(ኢ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው።
በዘርፉ ላይ ተወዳዳሪና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ለዘርፉ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና ህንጻ ተቋራጮች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የህንጻ ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የክህሎት፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ክፍተትን ለመሙላት እየተሰራ ያለውን ስራ ለአብነት አንስተዋል።
ይህንን ተከትሎ የሀገር ውስጥ ህንጻ ተቋራጮች በሀገር ውስጥ ህንጻዎችን ጨምሮ እየተገነቡ በሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ለኢንዱስትሪው ሽግግርና የቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ ሚና ባለው የቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴል ወይም(BIM) ላይ የህንጻ ተቋራጮች፣ የዘርፉ ምሁራንና ኢንዱስትሪዎች በቴክኖሎጂው ዙርያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማድረግና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል
የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል ትሬኒንግ የተሰኘው ስልጠናም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ለውጥ የሚያመጡ እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን የሚመሩ ባለሙያዎችም ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 89 ባለሙያዎች ስልጠናውን አጠናቀው አለም አቀፍ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ማረጋገጫ ወረቀት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026