አዲስ አበባ፤ ጥር 1/2017(ኢዜአ)፡- በሀረሪ ክልል ከ4 ሺህ 6 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም ገለፁ።
ኤጀንሲው በአምስት ሚሊዮን ኮደርስ መርሀ ግብር ስልጠና ከ4 ሺህ 6 መቶ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።
የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም የኮደርስ ስልጠናው የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማዳበር እንደ ሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማሳለጥ እንደሚያግዝ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተሰራው ስራ በክልል ደረጃ ስልጠናውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል 2 ሺህ የሚሆኑት የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።
በመርሀ ግብሩ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አንድሮይድና ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ሥልጠናው ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ስልጠናው ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል በሆኑ ስልጠናውን ያልወሰዱ በቀጣይ ግዜያት ተመዝግበው እንዲሰለጥኑ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ9 ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱንም ገልጸዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025