የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ካፒታል ገበያን የሁሉም ለሁሉም ለማድረግ በትኩረት ይሰራል - ሀና ተኸልኩ

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፦ ተአማኒነት ያለው፣ ሁሉን አሳታፊ እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን የሚፈጥር የካፒታል ገበያ ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልኩ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ትናንት በይፋ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይም የፓናል ውይይት ተካሂዷል።


በፓናሉ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልኩ ከዚህ ቀደም ለበርካታ ዓመታት የካፒታል ገበያ የሚመስሉ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት ከመንግስት የፖሊሲ አቅጣጫዎች፣ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም እና ከአጠቃላይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፎች በመነሳት የካፒታል ገበያ የማደራጀት ስራ ሲከናወን መቆየቱን አመልክተዋል።

በዚህም ትልቅ ትኩረት ግልጽ የሆነ የካፒታል ገበያን የሚመራና የሚቆጣጣር የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እንደነበር ጠቅሰው የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248 ጸድቆ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።


የህግ ማዕቀፉ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ እና ገበያውን የሚያገናኙ ተቋማት እንዲተዋወቁ ማድረጉ ነው ዋና ዳይሬክተሯ የገለጹት።

አዋጁ ገበያውን ለማቀላጠፍ የሚያመቹ ተቋማት እና ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ የሚያስችል የአሰራር ማዕቀፍ መዘርጋቱን አመልክተዋል።

በተለይም በኢንቨስትሮች መካከል በአካል ይደረግ የነበረውን የሙዓለ ሰነዶች ግብይት በቴክኖሎጂ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል።

አዋጁን ተከትለው የወጡ መመሪያዎች ኢንቨስተሮችን ይጎዱ የነበሩ ችግሮች ለመቅረፍ እና ለውሳኔ የሚያግዛቸውን በቂ እና ጥራታቸውን የጠበቁ መረጃዎች እንዲያገኙ የሚያስችል የአሰራር ማዕቀፍ መፈጠሩን አስረድተዋል።

ባለስልጣኑ በዋናነት የኢንቨስትመንት ጥበቃ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ነው ያነሱት።

በተጨማሪም ስለ ካፒታል ገበያ ለባለድርሻ አካላት ሰፊ የግንዛቤ የመፍጠር እና የማስተማር ስራ መከናወኑን ነው የገለጹት።

እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በቀጣይ በሙዓለ ሰነድ አቅራቢ ዋና ኢንቨስተሩ የሚታመን የካፒታል ገበያ ለመገንባት በትኩረት ይሰራል።


በካፒታል ገበያው የባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲኖር፣ በርካታ ምርቶች እና አገልግሎቶች ለገበያው እንዲቀርቡ እና ሁሉን አሳታፊ ለማድረግ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ካፒታል ገበያ የሁሉም ለሁሉም ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና የግሉ ዘርፍን ጨምሮ ሁሉም ሰው እንዲሳተፍ የሚያስችሉ አሰራሮች መኖራቸውን አንስተዋል።

በአጠቃላይ የካፒታል ገበያ የኢትዮጵያን ጥቅል ኢኮኖሚ የሚደገፍ እና የዜጎችን ህይወት የሚቀይር ዘርፍ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የተለያዩ የንግድ አይነቶችን ታሳቢ በማድረግ ሶስት ልዩ ልዩ የገበያ አይነቶችን የሚያቀርብ ነው።

እነርሱም የአክሲዮን ገበያ፣ የዕዳ ሰነድ ገበያ እና የአማራጭ ገበያ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025