ሐረር፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የስራ እድል እየፈጠሩ እና በኢኮኖ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የከተማው ነዋሪ አቶ ጣሂር ተፈራ፤ በከተማው በኮሪደር ልማት እየተከናወኑ የሚገኙ የእግረኛ መንገድ እና ሌሎች የልማት ስራዎች የከተማዋን ውበት ከመጨመር ባለፈ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተማዋን የሚመጥን የልማት ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተከናውኗዋል፤ እነዚህም ስራዎች የከተማዋን ውበት ከመጨመር ባለፈ ህዝቡ የእረፍት ጊዜውን የሚያሳልፍበት ስፍራ እንዲያገኝ አስችሏል ሲሉ የተናገሩት ደግሞ መምህር በፍቃዱ ታደሰ ናቸው።
ወጣት በቀለ በላይ ቀደም ሲል የቆሻሻ መጣያ የነበሩ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት ውብና ጽዱ ሆነው መዝናኛና መናፈሻ ስፍራዎች ሆነዋል፤ ይህም እጅግ አስደስቶናል እኔና መሰሎቼ እዚህ በመምጣት ትርፍ ጊዜያችንን እናሳልፋለን ሲልም ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማት ስራው ፍጥነትን ባማከለ መልኩ እየተከናወነና የከተማዋን ገጽታም እየለወጠ መሆኑን የተናገሩት በከተማዋ በኮሪደር ልማት በተገነቡ የመዝናኛ ስፍራዎች ፎቶ ግራፍ በማንሳት የሚተዳደሩት አቶ ተክሉ መታፈርያ ናቸው።
በከተማው የተገነቡ የኮሪደር ልማት ስራዎች ቀደም ሲል በከተማው ውስጥ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ የቀረፈ መሆኑን የጠቀሱት የከተማው መዘጋጃ ቤት ሰራተኛ የሆኑት ወይዘሮ እስከዳር ሃይሉ ናቸው።
በከተማው በኮሪደር ልማቱ በተገነባው ኑር ፕላዛ መናፈሻ ከሚዝናኑ ደንበኞች ማዘጋጃ ቤቱ ገቢ ማግኘት መጀመሩንም ጠቅሰዋል።
በክልሉ በሶስት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተከናወነ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ጥቅምት 22/2017 ዓ/ም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት መጀመሩ ይታወሳል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025