ጅማ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- ባለፉት አምስት ወራት 617 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ገለጹ።
በጅማ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የፋይናንስ፣ የፕላንና ገቢዎች የምክክር መድረክ ዛሬ በገቢ አሰባሰብ ላይ አተኩሮ ውይይት አድርጓል።
በዚሁ ጊዜ የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ፤ ባለፉት አምስት ወራት ለመሰብሰብ የታቀደው 648 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልጸው 617 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
ይህም ለመሰብሰብ ከታቀደው 95 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።
የበጀት ዓመቱን እቅድ ለማሳካትም የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት የደረሰኝ ማጭበርበርንና የታክስ ስወራን መከላከል ላይ በትኩረት እንዲሰሩም አሳስበዋል።
በተጨማሪም የግብር ከፋዩን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎችን ማጠናከር፣ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማገዝም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ነው ያሉት።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025