
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2017(ኢዜአ)፦መንግሥት ለግሉ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት በመጠቀም የመኖሪያ ቤት ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት መደረጉን የኦቪድ ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ ገለጹ።
የኦቪድ ሆልዲንግ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር እስከ 2030 ለማሳካት ያለመውን የአምስት ዓመት ሥትራቴጂክ ዕቅድ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ አጋርነትና ትብብር፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ እንዲሁም ብቃትና ለደንበኞች ትኩረት መስጠት የሚሉ መርሆዎችን የያዘ ነው።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው በመርሃ-ግብሩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ለደንበኞቻችን የገባነውን ቃል ኪዳን እና ለተሻለች ኢትዮጵያ እውን መሆን በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን በይፋ ባስጀመሩበት ማግስት ስትራቴጂው ይፋ መደረጉም መልካም አጋጣሚ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ በመንግሥት አነሳሽነት የተጀመረው የቤት ልማት አጋርነት ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ቁልፍ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።
በመሆኑም የግሉ ዘርፍ መንግሥት የሰጠውን ትኩረት በመጠቀም ለኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና ቁልፍ ሚናውን ሊጫወት ይገባል ብለዋል።
መንግሥት ለግሉ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት በመጠቀም የመኖሪያ ቤት ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየሰራን ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየው የቤት አቅርቦት ችግሮች በጥናት መለየታቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም በዘርፉ ላይ የታዩትን ሳንካዎች እንደ ችግር ከማየት ይልቅ ወደ መልካም አጋጣሚነት ለመቀየር ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል።
በዚህም የኦቪድ ሆልዲንግ 2030 ስትራቴጂ እውን ለማድረግ በመሰረታዊ ችግሮች ላይ የሚወሰዱ የመፍትሔ ርምጃዎች ላይ አተኩረን እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026