
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነት ክፍተትን ለማጥበብ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን ለመፍጠር እየተጋ እንደሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰለሞን ኩዋይኖርና የባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ሪጅን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሊያንድር ባሶሌ(ዶ/ር) ከተመራ ከፍተኛ ልዑክ ጋር በአፍሪካ የዲጂታል መጻኢ እድገት ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ ግዙፉ የቴሌኮም ኦፕሬተር እንደመሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነት ክፍተትን ለማጥበብ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ አካታችና ቀጣይነት ያለው እድገትን ለማምጣት እየተጋ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

አክለውም አፍሪካ ያሉባትን ተግዳሮቶች ለማለፍ፣ አዳዲስ ዕድሎችንና ዘላቂ ልማትን ለመፍጠር ቴክኖሎጂን እና ዲጂታል መፍትሔዎችን መጠቀም እንዳለባትም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ ዘርፈ ብዙ ጥረት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን ከማሳካት ባለፈ የአፍሪካ ዲጂታል አቅምን ለማጎልበት ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ የቴሌኮም ኢንዱስትሪውን በፋይናንስ መደገፍ ከትስስር ባሻገር አጠቃላይ የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ራዕይ ከግብ ለማድረስ የተለያዩ ፋይናንሰሮችን ጨምሮ ቁልፍ ዓለም አቀፍ አጋሮችን በመሳብ የበለጸገች ዲጂታል አፍሪካን ራዕይ እውን የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰለሞን ኩዋይኖር የኢትዮ ቴሌኮምን ፈጣን ዕድገትና ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እየተጫወተ ስለሚገኘው አስተዋፅኦ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸውን ጉዳዮች በማብራራት የአፍሪካ ልማት ባንክ የኩባንያውን ዲጂታል ኢኒሸቲቭ ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026