
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ቻይና ተጨማሪ መስኮችን በመለየት ጠንካራ የንግድ ትስስራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ አስታወቁ።
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በቻይና መንግስት ምክር ቤት የልማት ምርምር ማዕከል ፕሬዝዳንት ሉ ሃኦ ከተመራ ልዑክ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ ከልዑኩ ጋር በኢትዮጵያና ቻይና የንግድ ግንኙነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ወደ ላቀ ትብብር ማሸጋገር የሚያስችሉ መስኮች መለየታቸውን አመልክተዋል።
በተለይም ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ማሳደግና የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተጨማሪ መስኮችን የዳሰሰ ውጤታማ ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል።
ልዑኩ የጥራት መንደርን መጎበኘቱንና ኢትዮጵያ ለጥራት ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየት እንደተቻለም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026