አዲስ አበባ፤ ጥር 12/207(ኢዜአ)፦ በቦንጋ ከተማ ግንባታ እየተከናወነ የሚገኘው የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ ማዕከል ግንባታ 98 ከመቶ መድረሱ የኢትዮጵያ ግብርና ኮርፖሬሽን ገለፀ።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አማካሪ አቶ ካሳሁን ከበደ መንግስት ግብርናን ለማዘመን ከሚያደርጋቸው ጥረቶች መካከል የግብርና ግብዓቶችን በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ ለአምራቾች ተደራሽ የማድረግ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በደቡብ ምዕራብ ቀጠና ተደራሽነቱን በማስፋት በ2012 ዓ.ም ጀምሮ የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ ማዕከልግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በ742 ሚሊየን ብር ወጪ ግንባታ ላይ የሚገኘው ማዕከሉ 98 ከመቶ መድረሱን ገልጸው፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለአምራቾች የተሟላ የግብርና ግብዓትና የእርሻ ቴክኖሎጂ መሳሪያ ለማቅረብ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በቦንጋ ማዕከል በቀጠናው የጥራት ደረጃው የተሻሻሉ ምርጥ ዘር በማምራት ለማቅረብ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የማዕከሉ ግንባታ በሁለት ሎት ተከፍሎ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ግንባታው በውስጥ የተለያየ መጠን ያላቸው የእህል ማከማቻ መጋዘኖች፣ ማበጠሪያ ማሽን ክፍሎችና የተለያዩ የኬሚካል ማከማቻ፣ የአስተዳደር ሠራተኛ ቢሮ እንዲሁም የእርሻ ማሽነሪዎች ማከማቻና መስጫ ሼዶች በውስጡ ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል።
በኮርፖሬሽኑ የምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘነበ ወልደሰንበት በበኩላቸው ማዕከሉ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ በቀጠናው ተደራሽ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ እንዳለው መናገራቸውን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኮሙኒኬሸን ቢሮ ያገነኘው መረጃ ያመለክታል።
ኮርፖሬሽኑ የሰብል ዘርን በተለያዩ መንገድ በመሰብሰብ በማዘጋጀትና ደረጃ በማውጣት ለእርሶና ከፍል አርሶ አደሮች እንደሚያቀርብ የገለጹት ስራ አስፈጻሚው እንደሀገር በ2016/17 ምርት ዘመን 465 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ የተለያዩ የሰብል ዘር በማባዛት ለአምራቾች ለማቅረብ በ25 ቅርንጫፎቹ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025