አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ "ጋዲሳ ኦዳ" የተሰኘውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ጎበኙ።
አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዳማ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተናበበና በተቀናጀ መልኩ በአንድ ማዕከል ለመስጠት የተቋቋመውና "ጋዲሳ ኦዳ" የሚል ስያሜ የተሰጠውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ጎብኝዋል።
አሰራር ስርዓቱ 29 ሴክተሮችን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ በቴክኖሎጂ በተደገፈ አግባብ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ስርዓት የባለጉዳዮችን እንግልት የቀነሰ፣ ገቢን ለመሰብሰብ ምቹ የሆነ፣ ልማዳዊ የሆነውን የወረቀት ስርዓት ከ80 ፐርሰንት በላይ በሁሉም ሴክተሮች ውስጥ ያስቀረ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም የአሰራር ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከፍተኛ እድል የፈጠረ መሆኑን አይተናል ነው ያሉት።
የከተማ አስተዳደሩ በከተማ ደረጃ ያሉ ተቋማትን በአንድ ማዕከል ከማሰበሰብ ባሻገር የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ተቋማትም በአንድ ማዕከል እንዲሰሩ ማድረጉ እጅግ የሚበረታታ እና ለሌሎች ከተማ አስተዳደሮችም ተሞክሮ የሚሆን ነውም ብለዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አመታት በተሰሩ ስራዎች መሬትን ሙሉ ለሙሉ በካድስተር ቴክኖሎጂ ዲጅታል ለማድረግ የተሄደበት ርቀት፣ በከተማዋ የሚኖሩ ዜጎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል የተዘረጋው የሲሲቲቪ ካሜራ ዝርጋታ ውጤታማ እንደሆነ ተናግረዋል።
በቀጣይም በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በምርጥ ተሞክሮነት ተወስዶ ተግባራዊ እንዲደረግ እንደ ብልፅግና ፓርቲ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025