የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቀሌ ዲስትሪክት 70 በመቶ ደንበኞቹ ገንዘብ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያንቀሳቀሱ መሆኑን ገለጸ

Jan 22, 2025

IDOPRESS

መቀሌ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቀሌ ዲስትሪክት 70 በመቶ ደንበኞቹ ገንዘብ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እያንቀሳቀሱ መሆኑን አስታውቋል።

የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ልሳነወርቅ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባንኩ የሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ ሌሎች የቴክኖሎጂ አማራጮችን ዘርግቶ በማስተዋወቁ በርካታ ደንበኞቹን የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።

በዲስትሪክቱ በሚገኙ 58 ቅርንጫፎች ስር 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ደንበኞች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ኤልያስ፤ ከእነዚህ መካከልም 70 በመቶ ያህሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ገንዘባቸውን እያንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ገንዘብን ደህንነቱ በተጠቀ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።

እንዲሁም ፈጣን የግብይት አገልግሎትን በመፍጠር ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያስቻለ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

በተጨማሪም ደንበኞች ባሉበት ሆነው ሌሎች ስራዎቻቸውን እያከናወኑ ገንዘብ ለማስተላለፍም ሆነ የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም ቴክኖሎጂው እየረዳቸው መሆኑን አቶ ኤልያስ አመልክተዋል።

በቀጣዮቹ ወራትም የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ ደንበኞቹን ስለ አገልግሎቱ ያላቸውን ግንዛቤ ለማዳበር የተለያዩ የውይይት መድረኮችን ለማካሄድ እቅድ መያዙንም አስታውቀዋል።

የባንኩ የረጅም ጊዜ ደንበኛ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ መሀሪ ፍስሀ፣ ባንኩ የጀመረው የዲጂታል አገልግሎት የገንዘብ ዝውውር ጤናማነትን ስለሚያረጋግጥ መልካም መሆኑን ገልጸዋል።

አገልግሎቱ ፈጣንና አስተማማኝ በመሆኑም ስራቸውን እንዳቀለለላቸው የተናገሩት ደግሞ ሌላው የባንኩ ደንበኛ አቶ አሰፋ ገብረ ስላሴ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025