
ባህር ዳር ፤ጥር 28/2017 (ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ የኢንተርፕራይዞችን ምርት ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በስፋት ለማድረስና የገበያ ትስሰር መፍጠርን ዓላማ ያደረገ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ።
ጥርን በባህር ዳር አካል የሆነው የማጠቃለያ የኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ዛሬ ተከፍቷል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ እንደገለጹት፤ መንግስት የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ችግር ለመፍታት ከሰጣቸው ትኩረቶች አንዱ የገበያ ትስስር መፍጠር ነው።

ለዚህም ኤግዚቢሽኖችና ባዛሮችን በማዘጋጀት ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን ለተጠቃሚው ህብረተሰብ እንዲያቀርቡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የከተማው ህብረተሰብም በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚያመርቷቸውን ምርቶች በመግዛት ሊያበረታታ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘመነ አሰፋ በበኩላቸው "ለኢንተርፕራይዞች በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ ኤግዚቢሽንና ባዛር በማዘጋጀት ሸማችና ሻጩን በአንድ መድረክ በማገናኘት የገበያ ትስስር ለመፍጠር እየተሰራ ይገኛል " ብለዋል።

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 2 ቀን 2017 ዓም እንደሚቆይ ጠቁመው 47 ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ይዘው መቅረባቸውን ተናግረዋል።
በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ያመረቷቸውን ባህላዊ አልባሳት ይዘው መቅረባቸውን የገለፁት ደግሞ ወይዘሪት ነፃነት አጠቃ ናቸው።

በሦስት ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ከሦስት ዓመት በፊት የጀመሩት ስራ አሁን ላይ ካፒታላቸውን ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ማሳደጋቸውን ተናግረዋል።
ወጣት ይበልጣል በላይነህ በበኩሉ የሚዘጋጁ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች የገበያ ችግሮቻቸውን በትስስር ለመፍታት ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን ገልጿል።
በ2014 ዓ.ም በግማሽ ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል የጀመረው የጫማ ስራ አሁን ላይ ካፒታሉን 7 ሚሊዮን ብር ማድረሱን አስታውቋል።
የጥርን በባህር ዳር ማጠቃለያ በሆነው ኤግዚቢሽንና ባዛር በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና ሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ተሳትፈዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026