ዲላ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፡- በጌዴኦ ዞን በህብረተሰቡ ተሳትፎ ጭምር የህዝብን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
በዞኑ ዲላ ከተማ በ552 ሚሊዮን ብር ወጪ በከተማ አስተዳደሩ፣ በባለሀብትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ በዞኑ የህብረተሰቡን የልማት ተሳትፎ በማጠናከር የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ ነው።
በተለይ "ከህዝብ ለህዝብ" በሚል መርህ የመሰረተ ልማት ጉድለቶችን ለመሙላት በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን ነው የገለጹት።
ለዚህም ዛሬ በዲላ ከተማ የተመረቁትን ጨምሮ ዘንድሮ ብቻ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ለዓብነት ጠቅሰዋል።
መሰረተ ልማቶቹ የራስን አቅም አሟጦ መጠቀም ከተቻለ የዞኑን ልማትና ዕድገት በአጭር ጊዜ ማረጋጥ እንደሚቻል ማሳያ ናቸው ብለዋል።
ተጠናቅቀው ለአገልግሎት በበቁ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ለተሳተፉ የግል ባለሃብቶችና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላትም አስተዳዳሪው ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የተገኙ ልምዶችን በማስፋት በየደረጃው የህዝብን የልማት ፍላጎት ለማርካት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ተጠናቀው ለአገልግሎት የበቁት መሰረተ ልማቶች ከ552 ሚሊዮን ብር በላይ መፍጀታቸውን ጠቅሰው፣ የጌዴኦ የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓልን ምክንያት በመድረግ ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል።
በከተማው ዛሬ ለአገልግሎት የበቁት መሰረተ ልማቶች የከተማውን ደረጃ እንደሚያሳድጉ የገለጹት፣ ደግሞ የዲላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብነት አክሊሉ ናቸው።
ዛሬ ለአገልግሎት ከበቁት መሰረተ ልማቶች ስምንት የመማሪያ ክፍሎች፣ የኮሪደርና የአደባባይ ልማት፣ ንዑስ የፖሊስ ጣቢያ ግንባታ፣ የአገልገሎት መስጫ ቢሮዎች የሚገኙበት ሲሆን ሁሉም በተያዘው ዓመት ተጀምረው የተጠናቀቁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በልማቱ ከተሳተፉት ነዋሪዎች መካከል የዲላ ከተማ ነዋሪ አቶ የሱፍ ጠሃ በበኩላቸው፣ በዲላ ቆፌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አራት መማሪያ ክፍሎችን ገንብተው ማስረከባቸውን ገልጸዋል።
በትምህርት መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ መሳተፍ ትውልድን መቅረጽ ነው ያሉት አቶ የሱፍ፣ በተለይ በልጅነታቸው ለተማሩበት ትምህርት ቤት ድጋፍ በማድረጋቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
በቀጣይም በዲላ ከተማ የልማት ሥራ ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በመርሃ ግብሩ የዞኑና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025