የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በክልሉ ያለውን የመልማት አቅም በመለየት ለውጥ ለማምጣት ርብርብ ይደረጋል - ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

Feb 7, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ያለውን የመልማት አቅም በመለየትና በተደራጀ አግባብ በመምራት ለውጥ ለማምጣት ርብርብ እንደሚደረግ የክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ።

"ከእምቅ አቅም ወደ ሚጨበጥ ሃብት" በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ በቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚተገበሩ የልማት አቅጣጫዎች ታሳቢ ተደርጎ በተዘጋጀ የዕቅድ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የመሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ፤ ዕቅዱ በክልሉ በሁሉም ዘርፍ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በተደራጀ መልኩ ወደ ሀብትነት መቀየር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም ከሀገራዊው በተጨማሪ አዳዲስ ክልላዊ ኢንሼቲቮች መለየታቸውን አንስተው፣ በዚህም ያለንን አቅም በተገቢው ተጠቅመን ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በልዩ ትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

ክልሉ የሚታወቅባቸውንና ለሀገር ኢኮኖሚም ትልቅ ፋይዳ ያላቸው የቡና፣ የሻይ፣ ቅመማቅመም፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንሰት ልማት ማስፋትና ጥራቱን ማስጠበቅ ላይ በላቀ ቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉም ጠቅሰዋል።

የመስኖ ልማትን ማጠናከር፣ የአርሶና አርብቶ አደር ቁጠባን ማዳበር፣ የመሬት አስተዳደርን ማጠናከር፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት፣ የማዕድን ሀብቶችን በልዩ ንቅናቄ መምራት ከተያዙ አቅጣጫዎች መካከል እንደሚገኙበት አመላክተዋል።

በሚዘጋጁ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ሌላኛው ነው ብለዋል።

በዚህም ለሕዝቡ የገባነውን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር ተጠቃሚነቱን ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ በበኩላቸው፤ ክልሉ ያለውን ሀብት በተደራጀና አቅምን ባገናዘበ መልኩ ወደ ልማት ባለመገባቱ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት አልተቻለም ብለዋል።

ዕቅዱ ከተረጂነት የሚያላቅቅና እራሱን የሚለውጥ ማህበረሰብ የመፍጠር እሳቤ ያለው መሆኑን አመልክተው፤ በዚህም አርሶና አርብቶ አደሩ ሀብቱን ወደ ልማት በመቀየር ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።

ሰነዱ ያለንን ሀብት አውጥቶ ያሳየና ወደ ተሻለ ስራ የሚያስገባ ነው ያሉት ደግሞ የመድረኩ ተሳታፊ በብልፅግና ፖርቲ የካፋ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አጥናፉ ሀይሌ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በተበታተነ መልኩ ይሰራ የነበረውን በተደራጀ አኳን ለመተግባር ያስችላል ብለዋል።

ከዚህ አንፃርም እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በመለየት ውጤታማ በሚያደርግ መልኩ የተቀመጡ ተግባራትን ለመፈፀም ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025