የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የፕላስቲክ ፎርምወርክ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ

Feb 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፦የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ የፕላስቲክ ፎርምወርክ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካን መርቀው ስራ አስጀመሩ።

ፋብሪካው ገቢ ምርትን በመተካት በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ የማዳን አቅም እንዳለው ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት እንዳሉት ለአምራች ኢንዱስትሪ በልዩ ትኩረት የፖሊሲ እና የህግ ማእቀፎችን በማሻሻል ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

ለዘርፉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ምርትን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ መገንባት የሚቻለው ወደ ሀገር የሚገባ ምርትን የሚተኩ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው ፋብሪካም ተኪ ምርትን በማስፋትና የሀገራዊ ፖሊሲን በማሳካት ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።

ፋብሪካው በሀገራችን የእንጨት ፎርምዎርኮችን በፕላስቲክ መተካት መቻሉ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከመደገፍ አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል።

በተለይም የደን ጭፍጨፋን የሚታደግ እና የግንባታ ዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚጨምር መሆኑንም አመላክተዋል።

ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጪ ምንዛሬን በማዳን፣ ለዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ሚና ላላቸው ፋብሪካዎች ሚኒስቴሩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚና ባለቤት ካሳነሽ አያሌው በበኩላቸው፥ ፋብሪካው በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የግንባታ ፕላስቲክ ፎርምዎርክ አምርቶ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች እየተከለች ቢሆንም በሌላ በኩል ለእንጨት ፎርምዎርክ መስሪያ ዛፎች እንደሚቆረጡ አንስተዋል።

የፕላስቲክ ፎርምዎርኩ ከእንጨት የሚሰራ የግንባታ ግብዓትን በመተካት የደን መጨፍጨፍን ለመቀነስ እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።

ምርቶቹ በሀገራችን ውስጥ መመረታቸው ከውጭ የሚገባውን ተመሳሳይ ምርት በመተካት በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከአዲስ የፕላስቲክ ጥሬ እቃ በተጨማሪ የወዳደቁ የፕላስቲክ ውጤቶችን በግብዓትነት መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል በመሆኑ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025