የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያፋጥኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ

Feb 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን እድገትና ብልጽግና የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የመንገድ ዘርፍ ጉባዔ ዛሬ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።

በጉባዔው ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሠረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር)፣ የክልል የዘርፉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት መንግስት ለከተሞች በሰጠው ልዩ ትኩረት በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመንገድ ዘርፉን ለማሳደግና የገጠሩን ማህበረሰብ ከከተማ ነዋሪው ጋር ለማስተሳሰር የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል።

በዚህም የሀገርን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

በዚህም የመንገድ ሽፋንን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከለውጡ በፊት ከነበረበት 126 ሺህ ኪሎ ሜትር ወደ 171 ሺህ ነጥብ 18 ኪሎ ሜትር ማሳደግ መቻሉን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያን እድገት እና ልማት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላሉ ብለዋል ሚኒስትሯ በንግግራቸው።

በመንገድ ዘርፍ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማሳደግ እና ለህብረተሰቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ዘላቂነትንና ፍትሃዊነትን በየጊዜው በማረጋገጥ በ2030 ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ማዕከል ለማድረግ ይሰራል ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) በበኩላቸው መንግስት ለመንገድ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም የክልሉን የመንገድ ሽፋን በማሳደግ እድገትን ለማፈጠን እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

በፎረሙ የሀገር እና ክልል አቀፍ የመንገድ እና መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የቅንጅት አሰራርን ለማጠናከር ያለመ የመንገድ ዘርፍ ፎረም መመስረቱንም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025