
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፦ ስምንተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይከናወናል።
ፎረሙ የሚካሄደው “ከእመርታ ወደ ብልጽግና፤ የአፍሪካን ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች አቅም ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
የቢዝነስ ፎረሙ በአፍሪካ የቁም እንስሳት፣ ግብርና እና ፋርማሲዩቲካል ዘርፎች ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለት እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑን ኢዜአ ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
መንግስታት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ እሴትን በመጨመር፣ በዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያከናወኑት ያለው ስራ ውይይት ይደረግበታል።
ፎረሙ ለቀጣናዊ እሴት ሰንሰለት እና ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ልማት የኢንቨስትመንት ሀብት ማሰባሰብ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል።
የአፍሪካ የቢዝነስ ፎረም እ.አ.አ ከ2018 አንስቶ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ፎረሙ በመንግስታት፣ ባለሀብቶች፣ ፕሮጀክት አስተባባሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል የዘላቂ ልማት ግቦች እና የአጀንዳ 2063 ውጥኖችን ለማሳካት ያሉ እድሎች፣ ፈተናዎች እና ተግባራዊ ምላሾች ላይ እንዲወያዩ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ኮሚሽኑ ገልጿል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026