አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የህዝብን ውስን ሀብት በቁጠባና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለህዝብ አገልግሎት ተደራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተቋም እንዲሆን ምክር ቤቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ገልፀዋል።
ምክትል አፈ ጉባኤዋ የፌዴራል ዋና ኦዲተር 80ኛ አመት የምስረታ መታሰቢያ በዓልና የሕንጻ እድሳት ምረቃ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ለአንድ ሀገር እድገትና ብልጽግና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ተልዕኳቸውን የሚወጡ የመንግስት ተቋማት የሚያበረክቱት ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል።
በተለይም ለህብረተሰቡና ለሀገር የተለያዩ አገልግሎቶችን በማቅረብ የተጣለባቸውን ተግባርና ኃላፊነት የሚወጡ ተቋማት መንግስትና አሠራር በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተቋማት ለህገ ወጥ አሠራር እንዳይጋለጡና በጀትና ሌሎች ግብዓቶች ለብክነት ሳይጋለጡ፤ ህግና አሠራር ተከትለው ለሚፈለገው አላማ እንዲውል እንዲሁም ብልሹ አሠራሮች እንዲታረሙና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የተቆጣጣሪ ተቋማትን አቅም መገንባት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ተቋሙ በተሰጡት ስልጣንና ተግባሮች የተቋማትን የበጀትና ንብረት አጠቃቀም እና አያያዝ ህጋዊነት ነጻና ገለልተኛ በሆነ መርህ በማረጋገጥ የተጠያቂነትና የግልጽነት አሠራር እንዲሰፍን በማድረግ የበኩሉን ሚና ሲወጣ ቆይቷል ነው ያሉት፡፡
የተለያዩ ተቋማትን አሠራር በመቆጣጠርና በመመርመር እንዲሁም የታዩ የአሠራር ችግሮችን በተለያዩ ኦዲቶች ነቅሶ በማውጣትና እንዲስተካከሉ በማድረግ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራርን በማረጋገጥ ውጤታማ ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ የኦዲት አሠራር ወጥና አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ከፌዴራል ተቋማት አልፎ ሀገራዊ እንዲሆን ለማድረግና፤ ኦዲቱ የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ የሚያስችሉትን ቅንጅታዊ አሠራሮችን በመከተል ላይ እንደሚገኝም እንስተዋል።
ምክር ቤቱ ተቋሙ ተልዕኮውን ለማሳካት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አስፈላጊውን እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
በመርሃ ግብሩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ መሠረት ኃይሌ፣ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት፣ የተለያዩ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025