የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማ ነው

Feb 11, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ወራት ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ገለጹ።

የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሒዷል።

ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ ባለፉት ስድስት ወራት ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማ እንደነበር ገልጸዋል።

በቀሪው ግማሽ አመት በታክስ ፖሊሲ አፈጻጸም፣ በውጭ ሀብት አሰባሰብ፣ በዕዳ ማሸጋሸግ የጋራ ማዕቀፍ አፈጻጸሞች፣ በጥሬ ገንዘብ ፍሰት ማኔጅመንትና በበጀት ዝግጅት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለጹት ያለፉት ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደርጎ የኢኮኖሚ ማነቆ የነበሩ ችግሮች እልባት እያገኙ የመጡበት ነው ብለዋል፡፡

ይህ ተስፋ ሰጪ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው አመራሩና ሰራተኛው ተቀናጅቶ በመስራቱ በመሆኑ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በስድስት ወራቱ የስራ አፈፃፀም ግምገማ የገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የሆኑት የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን፣ የመንግስት ግዢ አግልግሎትና የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025