የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

<p>ሳይፈቀድላቸው በአዲስ አበባና አካባቢዋ ድሮን በሚያስነሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው - ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት</p>

Feb 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፦ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ሳያገኙ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ድሮን በሚያስነሱና በሚያበሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የድሮንና ሌሎች በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ማንኛውንም አይነት ድሮን ያለ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል በቅርቡ በመገናኛ ብዙኃን የተላለፈውን ማሳሰቢያ በማያከብሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማንኛውንም አይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር አይቻልም

በተለይ ከአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር ተያይዞ ቅንጅታዊ ስምሪቱን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ማንኛውንም አይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል መልዕክት የተላለፈ መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፤ ብዙዎችም ይህን ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ጠቁሟል፡፡


ማሳሰቢያውን በመጣስ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮን ለማስነሳትና ለማብረር ሙከራ ያደረጉ አካላትን በጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ በመለየት ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ ከማድረግ ጀምሮ ተገቢው እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የመሪዎችን፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን እና ብሔራዊ ኩነቶችን ደኅንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጿል።

በተለይ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ድሮኖችና መሰል ቴክኖሎጂ ወለድ መሣሪያዎች የሚፈጥሯቸውን ስጋቶች ለመከላከል የሚያስችል በቂ የቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል ዝግጅት አድርጎ ወደ ስምሪት መግባቱን አስታውቋል፡፡


ከሥራ ጋር በተያያዘ ድሮኖችን መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም አካል በ+251 983 00 02 98 እና +251 983 00 04 01 ስልክ ቁጥሮች በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት እንደሚችል አገልግሎቱ አሳስቧል።

ያለፍቃድ በሚነሱ እና በሚበሩ ድሮኖች ላይ የሚደረገው ቁጥጥርና የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክቷል፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026