የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ኢንስቲትዩቱ 32 ዕጩ የሰብል ዝሪያዎች በምርምር አወጣ

Feb 13, 2025

IDOPRESS

አዳማ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በተያዘው ዓመት የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዙ 32 ዕጩ ዝሪያዎች በምርምር ማውጣቱን ገለጸ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ቦጋለ ለኢዜአ እንደገለፁት ኢንስቲትዩቱ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በምርምር በማውጣት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ ነው።

በተለይ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር የእርሻ ስራ ማዘመን የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽ እየተደረጉ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት በኢኒሼቲቭ መልክ እየተገበራቸው የሚገኙ የበጋ መስኖ ስንዴ፣ የቢራ ገብስ፣ የሩዝ ልማትን ጨምሮ ሌሎች የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል በኢንስቲትዩቱ ተደራሽ የተደረጉ ቴክኖሎጂዎች ውጤት እያመጡ መሆኑንም ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት ብቻ ከ400 በላይ ግብርናን የሚያዘምኑ የምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎችን ኢንስቲትዩቱ በምርምር ማውጣቱን ጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ ዘንድሮም በእስከ አሁኑ ሂደት 32 ዕጩ ዝሪያዎች በምርምር ወጥተው በብሔራዊ ኮሚቴ እንዲፀድቁ ለውሳኔ ቀርበዋል ብለዋል።

ከወጡት ዕጩ ዝሪያዎች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውን የተሻለ ምርት የሚሰጡ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ቦቆሎ ማሽላና ጥራጥሬ ሰብል ዝርያዎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

የምስራቅ ቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን በዞኑ ሕዝቡ ወደ ከፊል አርብቶ አደርነት እንዲሸጋገር ለማስቻል እንዲሁም በተደጋጋሚ በአካባቢው የሚከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም፣ የመጠጥና የመስኖ ውሃ እጥረት ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም 'ፊና ኦሮሚያ' በተሰኘ የክልሉ መንግስት ፕሮጀክት አማካኝነት አራት ትላልቅ የመስኖና መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር እየተገነቡ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025