አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት አመት በስድስት ወራት ውስጥ 61 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በበጀት አመቱ ስድስት ወራት በቴሌ ብር አማካኝነት አንድ ትሪሊዮን ብር ዝውውር መፈፀሙን ገልጸዋል።
ወጪ ቆጣቢ የዲጂታል አገልግሎትን ተግባራዊ በማድረግ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉንም አብራርተዋል።
እንደ ሀገር ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሒደት ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም ትልቁን ድርሻ ወስዶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በዚህ ረገድ ኢትዮ ቴሌኮም ለሶስት አመት የሚተገበር አምስት ግቦች ያሉት ስትራቴጂክ እቅድ ነድፎ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
የአገልግሎት ጥራት፣ የገቢ ምንጭ ማስፋት፣ አዳዲስ የስራ እድል መፍጠር፣ ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት መስጠትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን መፍጠር የስትራቴጂክ ዕቅዱ አካል መሆናቸውን አብራርተዋል።
ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት 202 በሚሆኑ አካባቢዎች አዳዲስ የገመድ አልባ አገልግሎቶችን ማስፋት መቻሉንም ጠቅሰዋል።
በስምንት ከተሞች ላይ የ5ኛ ትውልድ ወይም 5ጂ ኔትወርክ አንዲሁም 67 ከተሞችን የ4ኛ ትውልድ ወይም 4ጂ ኔትወርክ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ አገልግሎት የተቋረጠባቸው አካባቢዎችን ዳግም ወደ አገልግሎት ለማስገባት በተሰራው ስራ 216 አካባቢዎች ሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አብራርተዋል።
ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ተቋሙ ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት 61 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታውቀዋል።
ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ43 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ነው የተናገሩት።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025