የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በጋምቤላ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የአፈር ማዳበሪያ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው - ቢሮው

Feb 14, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በመጪው የመኸር እርሻ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፈር ማዳበሪያ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በምርት ዘመኑ ከ172 ሺህ 230 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

በጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የእርሻ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳግም ምላሽን ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ በ2017/18 የምርት ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ሙሉ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል።

ከአሁን በፊት ለክልሉ አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች የምርት ማሳዳጊያ ግብዓት በተሟላ መልኩ አለመቅረቡ በምርት እድገቱ ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮ መቆየቱን ጠቁመው፤ በዘንድሮው የምርት ዘመን የግብዓት ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በተለይም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ግብርናውን በቴክኖሎጂ መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም በዘንድሮው የመኸር እርሻ በክልሉ የአፈር ማዳበሪያን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ በማዋል ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ወደ ክልሉ 60 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መግባቱን ጠቁመው፤ የአርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች እንዲሁም የባለሃብቶች ፍላጎት እየታየ የግብዓት አቅርቦቱ እንደሚጨምር አስረድተዋል።

በምርት ዘመኑ በክልሉ ከ172 ሺህ 230 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

አሁን ላይ እቅዱን ለማሳካት ከማዳበሪያ ግብዓት አቅርቦት በተጨማሪ ከ5 ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ፣ የማሽላ፣ የሩዝና ሌሎች የምርጥ ዘር ግብዓትና የእርሻ ትራክተር ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ በመጪው የመኸር እርሻ ለማልማት የታቀደው መሬት ካለፈው ዓመት በስድስት ሺህ ሄክታር፤ በምርት መጠን ደግሞ ከ400 ሺህ ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው እንደሆነ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አመላክተዋል።

በቢሮው የምርት ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክተር አባላ ኡቦንግ(ዶ/ር) በበኩላቸው ግብዓት መቅረቡ ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የታለመውን ግብ ለማሳካት የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025