አዲስ አበባ፤የካቲት 9/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ውስጥ መግባቷን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ንጎዚ ኦኮንጆ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፥ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል በመሆን ሂደት ውስጥ አመታትን ማስቆጠሯን ገልጸዋል።
የአባልነት ሂደቱን ለማሳካትም በቀጣይ ሊደረጉ ሊወሰዱ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ መወያየታቸውን በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በቀጣይ ሊደረጉ የሚገባቸው አስፈላጊ መስፈርቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአለም ንግድ ድርጅት አባልነትን ከብሄራዊ ጥቅማችን ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ውስጥ መግባቷን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን ብለዋል።
አክለውም፥ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነቱን ለማፋጠን፥ ኢትዮጵያ በአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እያስመዘገበች ያለው እድገት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025