
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካን ዕድገት የሚያፋጥኑ ከ70 በላይ ታላላቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽን ገለጸ።
ተሰናባቿ የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር አማኒ አቡዜይድ በአፍሪካ እየተከናወኑ የሚገኙ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም፥ በአህጉሪቱ እ.አ.አ ከ2021 ጀምሮ ከ70 በላይ ዕድገትን የሚያፋጥኑ ታላላቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
አህጉሪቱ አንድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት በአፍሪካ ከሚከናወኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑንም አስረድተዋል።
በ2023 ይፋ የተደረገውን የአንድ አፍሪካ አየር ትራንስፖርት መርኃ ግብር ተከትሎ 39 የአህጉሪቱ ሀገራት መርኃ ግብሩን መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአህጉሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማሳለጥ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ገንቢ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በ2017 የተጀመረውን የታዳሽ ኃይል አቅርቦት መርኃ ግብር መነሻ በማድረግ አህጉሪቱ በታዳሽ ኃይል ልማት ተጠቃሚ እንድትሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በአፍሪካ በቂ የኃይል አቅርቦት ባለመኖሩ የታዳሽ ኃይል አቅርቦት ልማት መርኃ ግብሩ ችግሩን ለመፍታት ገንቢ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በታዳሽ ኃይል አቅርቦት መርኃ ግብር ከአየር ንብረት ተጽዕኖ የጸዳ ሃይል ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በ2021 የተጀመረው የአፍሪካ ዲጂታል ስትራቴጂ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋትን ዳታ እንድታመነጭ እና ከሳይበር ጥቃት ራሷን እንድትከላከል ያለመ እንደሆነም አንስተዋል።
አፍሪካን እርስ በእርስ የሚያስተሳስረው የባቡር መሥመር ዝርጋታ በአህጉሪቱ ከሚከናወኑ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ የአፍሪካን ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀዋሳ ከተማን በማልማት የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Jun 14, 2026
ጋምቤላ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ...
Jun 11, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማ...
Jun 4, 2026
ዲላ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ከ40 በላይ የንግድ ተቋማትና አጋር አካላት ተሳትፈውበት በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችን እና የኢ...
May 25, 2026