የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ

Feb 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(ተመድ) የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ከፈተ።

ጥምረቱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ለዘላቂነት ልማት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት በዓለም ዙሪያ ያሉ የፈጠራ ልሂቃንና የቴክኒክ ባለሙያዎች ያሰባስባል።

በአዲስ አበባ የተከፈተው የጥምረቱ ቢሮም የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት የሚሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን ያቀርባል ተብሏል።

የጥምረቱ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጀፍሪ ሳክስ እንዳሉት፣ የጥምረቱ ተቀዳሚ ዓላማ በዓለም ላይ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እና ማህበራዊ ፍትህ ማስፈን ነው።

መንግስታትን መደገፍ ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መፍትሔ በማፈላለግ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል።

በአዲስ አበባ በይፋ የተከፈተው የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ቢሮም አፍሪካ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መስራት የዓለም ስልጣኔ ፈርቀዳጅ መሆኗን የገለጹት ጀፍሪ ሳክስ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች መሆኑንም ተረድቻለሁ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) የዘላቂ የልማት ግቦች የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ን ከግብ ለማድረስ ቁልፍ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጥናትና ምርምር የላቀ አገልግሎት እንዳለው የገለጹት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረቱ ተጨማሪ አቅም ስለሚሆነው በትብብር እንሰራለን ለዚህ ደግሞ ቁርጠኛ ነን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025