
አዲስ አበባ፤የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦የኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉና በቴክኖሎጂ የተደገፉ የምርምር ውጤቶች ተግባር ላይ እንዲውሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ፡፡
የቴክኖሎጂ ምርምር ውጤቶች ወደ ተግባር ተለውጠው ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪና ኢኮኖሚ አድገት እንዲውሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ዘጠነኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ "ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ለኢንዱስትሪ" በሚል መሪ ሃሳብ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጄ እንግዳ በወቅቱ እንደገለጹት፥ ዓለም አንድ በሆነችበት በዚህ ዘመን እድገትና ልማትን ያለ ቴክኖሎጂና ሳይንስ ማሰብ አይቻልም፡፡
ኢትዮጵያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንቨስት ማድረጓ በምግብ ራሷን ለመቻል፣ዘላቂ የሃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ ፣ የጤና ስርአቱን ለማሻሻልና ኢንዱስትሪውን ለማዘመን ወሳኝ ጉዳይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው የቴክኖሎጂ ምርምሮች ወደ ተግባር ተለውጠው የአገሪቱን ኢኮኖሚ እና እድገት እንዲያፋጥኑ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አጋር አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው የተለያዩ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶችንና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማውጣት ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አብርሃም ደበበ በበኩላቸው፥ ዩንቨርስቲው ስድስት የልህቀት ማዕከል በመገንባት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር የሚያከናውናቸው ተግባራት ውጤት እያሳዩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኦስትሪያ አምባሳደር ዶክተር ሲሞን ናብ የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ለአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ በመሆናቸው በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የኦስትሪያ ዩንቨርስቲዎች ከኢትየጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በጉዳዩ ላይ በጋራ በርካታ ተግባራት እያከናወኑ ሲሆን በቀጣይም የሚሰሩት ስራ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባን ዘመናዊና ስማርት ሲቲ በማድረግ ሂደት ዩኒቨርስቲው ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የገለጹት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ቱሉ ጥላሁን ናቸው፡፡
በከተማዋ በሚሰሩ የቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች ከዩኒቨርስቲው ጋር በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026