መቀሌ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፡- በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላምን በማስፈንና እምቅ የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማልማት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገልጿል።
የክልሉ ኢኮኖሚ ያለበትን ሁኔታ እና ማተኮር በሚገቡ አቅጣጫዎችን የተመለከተ ፎረም በመቀሌ ተካሂዷል።
በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ካህሳይ በርሄ(ዶ/ር) የውይይት መነሻ ፅሑፍ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፤ የክልሉን ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ለማሳደግ ምቹ ሁኔታን መፍጠር እና ሰላምን ማጠናከር ይገባል።
ክልሉ የበርካታ ፀጋዎች ባለቤት መሆኑን ጠቁመው በተለይ በግብርና፣ በማዕድንና በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ሰላምና መረጋጋትን ማጠናከር ወሳኝ ነው ብለዋል።
በአጠቃላይ የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሲቪል ሰርቫንቱን ጨምሮ የአሰራርና የተቋማት ሪፎርም ትግበራዎችን ማከናወን አስፈላጊ እንደሆነም ጨምረው አመላክተዋል።
በኢንስቲትዩቱ የኢኮኖሚ ምሁር አርዓያ መብራህቱ(ዶ/ር) በበኩላቸው የክልሉን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት ዘርፎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።
በፌዴራል መንግስት እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች መጠናከር ወሳኝ መሆኑን አንስተው የክልሉን እምቅ ሃብት የማልማትና የመጠቀም ስራ ሊጠናከር ይገባል ነው ያሉት።
የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠልና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንም በላይ የክልሉን ሰላም ለማፅናት በትብብርና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
በክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የማህበራዊ ትስስርና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት አለብን ያሉት ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የኢኖቬሽን፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ከላሊ አድሀና(ዶ/ር) ናቸው።
ለሁለንተናዊ እድገት ሁለንተናዊ ጥናትና ምርምር ማካሄድ እንዲሁም መሰል የምክክር መድረኮችን አጠናክሮ ማስቀጠል የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዱም የውይይቱ ተሳታፊዎች አመልክተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025