ሮቤ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- በባሌ ዞን ባለፉት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ተግባራዊ በተደረጉ የልማት ኢኒሼቲቮች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ማስገኘታቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሐኪም አልይ ገለጹ።
አቶ አብዱልሐኪም አልይ ለኢዜአ እንዳሉት በዞኑ ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል መንግስት በተቀረጹ የግብርና ልማት ኢኒሼቲቮች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግቧል።
በዞኑ ስንዴን በክላስተር ማልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነብ እንዲሁም በቡና ልማት ዘርፍ አርሶ አደሩ የተሻለ ውጤት ያገኘባቸው ዋና ዋና ኢኒሼቲቮች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተለይ አርሶ አደሩ በኩታ ገጠም አሰራር ዘዴ ውጤታማ በሆነ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው በዚህም የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባሻገር ገቢውም እንዲያድግ እያገዘው ነው ብለዋል።
በዞኑ በመኽሩ ወቅት ከ580ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ መልማቱን አስታውሰዋል።
ከዚህ መካከል 250ሺህ ሄክታር መሬት የተሻሻለ የግብርና አሰራርና በመተግበር በስንዴ የለማ መሆኑን ጠቁመው ከ16 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱንም በማሳያነት አቅርበዋል።
በዞኑ ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በዚህ ዓመት ብቻ ከ110ሺህ የሚበልጡ ላሞችን በሰው ሰራሽ ዘዴ ለማዳቀል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ባለፉት ዓመታት የተፈጥሮ ኃብት ልማት ሥራ የተከናወኑባቸው አካባቢዎች ወጣቶችንና አርሶ አደሩን በማህበራት በማደራጀት በማር ምርት ኢኒሼቲቭ እንዲሰማሩ ከ85ሺህ የሚበልጡ ዘመናዊ ቀፎዎች ተሰራጭተዋል ብለዋል።
ከበጋ መስኖ ልማት አንጻርም በዞኑ 188ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት ስራው በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የተጀመረው ስራ ወጥነት ባለው መልኩ በሁሉም አርሶ አደሮች ተግባራዊ እንዲደረግ የግብርና ባለሙያው በንቃት እንዲሳተፍ ይደረጋል ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025