አዳማ፤ የካቲት 11/ 2017(ኢዜአ)፡- በአዳማ ከተማ የህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል እንዲጎለብትና የፋይናንስ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ ገለፁ።
አስተዳደሩ የቁጠባ ባህል ለማሳደግ የጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም የኢንተርፕርነሮችን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከሲንቄ ባንክ ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል እንዲጎለብትና የስራ ባህል እንዲለወጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በተለይ የከተማው ነዋሪ ሰርቶ መለወጥ እንዲችል ኢንተርፕርነርሽፕና የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የልማት ስራዎችን ለማፋጠን ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰው
የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች የስራ ባህልና አስተሳሰብ መለወጥ እንደሚገባም አክለዋል።
የቁጠባ ባህልን በማሳደግ በመቆጠብ ወደ ስራ መግባትና ራሳን መለወጥ እንዲቻል ከባንኩ ጋር ስምምነት መፈረሙን ገልጸዋል።
ተጠቃሚው ብድሩን በወቅቱ እንዲመልስ በየደረጃው የሚገኘው ባለድርሻ አካላትና አመራሮች በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበው አስተዳደሩ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል።
የሲንቄ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ነዋይ መገርሳ በበኩላቸው ባንኩ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ጨምሮ የገጠሩን ማህበረሰብ በማቀፍ አመርቂ ለውጥ እያመጣ ይገኛል ነው ያሉት።
የህዝቡ የቁጠባ ባህል እንዲጎለብትና ብድር ወስዶ ተጠቃሚ በመሆን በወቅቱ መመለስ እንዲችል በየደረጃው ክትትል መደረግ አለበት ሲሉም ገልጸዋል።
ባንኩ የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን በመቅረፍ በስራ ዕድል ፈጠራ፤ በሊዝ ማሽን አቅርቦት፤ በኢንቨስትመንት ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
ድህነትንና ስራ አጥነትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ባንኩ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025