ደሴ ፤ የካቲት 12/2017(ኢዜአ)፡-በደሴ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የከተማዋን ዕድገት በማፋጠን የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ መሆናቸው ተገለጸ።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን በደሴ ከተማ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ፣ የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር በደሴ የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የከተማውን እድገት የሚያፋጥኑ በመሆናቸው የሚበረታቱና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው ናቸው ብለዋል፡፡
የ"ኦን ላይን" አገልግሎት፣ "ስማርት ሲቲ" ፣ የአስፋልት መንገድ፣ የአውቶቡስ መናኸሪያ ፣ ኮሪደር ልማትና ሌሎችም በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዙ ተግባራት በከተማው መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።
ይህም ከተሞችን ለማሳደግና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ መንግስት ያስቀመጠው አቅጣጫ በትክክለኛው መንገድ ስለመተግበሩ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
በከተሞች የሚገነቡ መሰረተ ልማቶችን በቴክኖሎጂ ዲጅታላይዝድ በማድረግ ለህጻናትና ለአረጋዊያንም ጭምር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የደሴ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም አበራ በበኩላቸው፤ በከተማው የመሰረተ ልማትን በማሟላት ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በስማርት ሲቲ፣ በኮሪደር እና በሌሎችም መሰረተ ልማቶች አበረታች ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው፤ የፌዴራልና የክልሉ መንግስት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም አመልክተዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025